ብቸኛ ስለነበርኩ 38ሺህ ሴቶች ያሉበት የራሴን ማኅበረሰብ ፈጠርኩ

በ2022 መጀመሪያ ላይ ነበር፣ በለንደን ሌላ ጨለማ ቀን። ሎቪና ሼኖይ በማታውቀው እና አንዳንዴም በአስደናቂ ሁኔታ ውስጥ እየሄደች ለከተማዋ አዲስ ነበረች።
የ39 ዓመቷ ሎቪና ለቢቢሲ ስትናገር "ሕንድ፣ ቤተሰቦች አሉ፣ የትምህርት ቤት እና የኮሌጅ ጓደኞች አሉህ፣ ድጋፍ ብትፈልግ ሰው አለ በጥቅሉ የምቾት ዞን ውስጥ ነበርክ" ትላለች።
"ነገር ግን ወደ አዲስ አገር ስትመጣ በድንገት ትቀራለህ። ብቻህን ትሆናለህ"
ባብዛኛው ውጭ አገር በሚኖሩ የሕንድ ማኅበረሰብ ተከባ በዱባይ አስር ዓመታትን አሳልፋለች፤ ከዚያ በፊት ደግሞ በትውልድ ከተማዋ ሙምባይ ትኖር ነበር።
የትዳር አጋሯ አዲስ ሥራ በማግኘቱ ወደ ለንደን መሄድ አስደሳች ነበር። ነገር ግን 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሚኖሩባት ከተማ ውስጥ ብትሆንም፣ ባይተዋር ነበረች።
ሎቪና ሴት ጓደኞች እንዲኖሯት ትመኝ ነበር። ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር ባላት ኑሮ ደስተኛ ብትሆንም ነፍስያዋ የጎደለ ነገር እንዳላት ይነግራት ነበር።
'የራሴን ጎሳ አገኘሁ'

ሎቪና "ወደ ለንደን በሄድኩ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ፀሀይ 10 ሰዓት አካባቢ መጥለቅ እንደምትጀምር ተረዳሁ" ስትል ትቀልዳለች። "ብቸኝነት እና ድባቴ ውስጥ እገባለሁ ብዬ ሰግቼ ነበር። ምንም ጓደኛ አልነበረኝም"
እናም በግል የፌስቡክ ገጿ ላይ "ሰላም ሎቬና እባላለሁ፤ ከሙምባይ ነኝ፤ ወደ እዚህ [ለንደን] ከመምጣቴ በፊት በዱባይ ለአስር ዓመታት ኑሬያለሁ፤ አንድ ሲኒ ቡና አብሮኝ መጠጣት የሚፈልግ አለ");