BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የድንበር አካባቢዎች ምን አዲስ ነገር አለ?
ከሰሞኑ የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ክልል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች ለቅቆ ስለመውጣቱ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ሲሠራጭ ቆይቷል። ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኙ የክልሉ አካባቢዎች ክፍት ስለመሆናቸውም ሲነገር ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች እና ምንጮች ግን የኤርትራ ሠራዊት አሁንም አካባቢዎቹን ለቅቆ እንዳልወጣ ገልጸዋል።
ቪዲዮ, ማክሮን በአደባባይ የተገፈተሩት 'ለቀልድ' እንጂ የቤት ውስጥ ጸብ አይደለም አሉ, ርዝመት 0,35
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጉብኝት ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የሆነው በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ፕሬዝዳንቱ ፊት ለፊት በሚታዩበት ጊዜ አንድ እጅ ጸብ በሚመስል ሁኔታ ፊታቸውን በኃይል ሲገፋ ታይቷል። በዚህ ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ምንም እንዳልተፈጠረ የእጅ ሰላምታ ሰጥተው ሚስታቸውን ከጎናቸው በማድረግ ከአውሮፕላኑ ወርደዋል።
በትግራይ በተካሄዱ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ የቀረበባቸው ኮሎኔል ተወልደ ምን ይላሉ?
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በቅርቡ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የወርቅ ማዕድን ማውጣት ላይ ተሰማርተዋል ሲሉ ከከሰሷቸው የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸው መካከል የትግራይ ኃይሎች የመረጃ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ኮሎኔል ተወልደ ገብረትንሳዔ አንዱ ናቸው። ቢቢሲ ትግርኛ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ስማቸው የተጠቀሰውን ኮሎኔል ተወልደን ያናገረ ሲሆን፤ እሳቸውም "ስሜ ጠልሽቷል" ሲሉ የቀረበባቸውን ውንጀላ አስተባብለዋል።
ኤአይ ያፈቅራል? ያዝናል? የኅልውና ስጋት ነው?
ሰው ሠራሽ አስተውሎት በሰው ልጆች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖረው እንደሚችል እየተነገረ ነው። በተጨማሪም ‘ሰዋዊ’ ሊባሉ የሚችሉ ድርጊቶች ሊከውንም ይችላል እየተባ ሲሆን፣ አንዳንዶች ለሰው ልጆች ህልውና ስጋት ነው ይላሉ። ዕለት ከዕለት እየተራቀቀ የመጣው ሰው ሠራሽ አስተውሎት ማፍቀር እና ማዘንን የመሳሰሉ የሰው ልጆች ውስጥ የሚፈጠሩ ስሜቶችን ሊያሳይ ወይም ሊላበስ ይችላል?
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በነጻነት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ ኢትዮጵያ ምን አሉ?
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥታቸው እና ሕዝባቸው የኢትዮጵያን ለውጥ በመደገፋቸው እንደማይጸጸቱ ገልፀዋል። "የኤርትራ ሕዝብ እና መንግሥት ያልተቆጠበ ድጋፍ በማድረጉ እና ድንገት በተፈጠረ ለውጥ ምክንያት አይቆጩም" ያሉት ፕሬዚደንቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጠንካራ ትችቶች ሰንዝረዋል።
በኢትዮጵያ በአንድ ጨቅላ ላይ የተገኘው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? እንዴትስ ይተላለፋል?
በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ኤምፖክስ) የተያዘ ጨቅላ ሕጻን መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቀዋል። በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ የተገኘው የ21 ቀን ዕድሜ ባለው ጨቅላ ላይ ሲሆን እናቱም ለቫይረሱ መጋለጧ ተገልጿል።
በእስራኤል ጥቃት ዘጠኝ ልጆቹ የተገደሉበት አባት ህይወቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተነገረ
በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማዊ ዶክተር ባለቤት የሆነው እና እስራኤል አርብ ዕለት በፈጸመችው ጥቃት ልጆቹ የተደሉበት አባት ህይወቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ህክምና የሚያደርግለት ሆስፒታል ገለጸ።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አነጋጋሪ ጉዳይ
የአሜሪካ ኤምባሲ፤ መንግሥት "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጽማቸውን የድሮን ጥቃቶች "በአፋጣኝ እንዲያቆም" የጠየቀበትን ልጥፍ አሻሻለ
የአሜሪካ ኤምባሲ፤ ከሰዓታት በፊት አውጥቶት የነበረውን እና አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ የፌደራል መንግሥት "በራሱ ሕዝብ ላይ" የሚፈጽማቸውን የድሮን ጥቃቶች "በአፋጣኝ እንዲያቆም" ጥሪ ያቀረቡበትን ልጥፍ ከፌስቡክ እና ከቲውተር ገጾቹ ላይ አንስቶ ለውጥ አደረገ።
ኢትዮጵያውያን ጉምቱ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሩዋንዳ የሚፈልሱት ለምንድን ነው?
የካበተ ልምድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተፈላጊ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የምሥራቅ አፍሪካዋ ትንሽ አገር ሩዋንዳ ኢትዮጵያውያኑን በመሳብ አንዷ ለመሆን ችላለች። በአገሪቱ ከመንግሥት ተቋማት ጀምሮ በትላልቅ ሆስፒታሎች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በኃላፊነት ጭምር እየሠሩ ይገኛሉ። ታዲያ ኢትዮጵያውያኑን ሙያተኞች ወደ ሩዋንዳ የሚስባቸው ምን ይሆን?
እየናረ ለመጣው የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ምክንያቱ ምንድን ነው? በቅርቡስ ይቀንስ ይሆን?
ባለፉት ዓመታት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። በዚህም ሳቢያ በርካቶች ቀደም ሲል ሲመገቡ የነበሩትን የምግብ ዓይነቶች ለመቀየር ወይም በቀን የሚመገቡትን የምግብ መጠን እና ድግግሞሽ ለመቀነስ ተገድደዋል። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች እየቀረቡ ሲሆን፣ የዋጋ መናሩ ሊቀንስ የሚችልበት ዕድል ይኖር ይሆን?
የውጭ ዜጎች በሊዝ የቤት እና የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል?
የኢትዮጵያ መንግሥት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት እንዳይሆኑ ዕገዳ ጥሎ የነበረውን ሕግ የሚሽር አዋጅ አርቅቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። "የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ" የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበው ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት ሚያዝያ 23/2017 ዓ.ም. ነበር።
የጤና ባለሙያዎች የሥራ ማቆም አድማ በኢትዮጵያ ሕጎች እንዴት ይታያል?
የደሞዝ እና ሌሎች የሥራ ሁኔታቸው እንዲሻሻል በመጠየቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት ከፊል የሥራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ይህንንም ተከትሎ ድርጊቱን የተቃወሙ የጤና ባለሥልጣናት ማስጠንቀቂያ ከመስጠታቸው ባሻገር፤ በርካታ የጤና ባለሙያዎች በፀጥታ ኃይሎች ታስረዋል። ይህ የጤና ባለሙያዎች የሥራ የማቆም አድማ በኢትዮጵያ ሕጎች እንዴት ነው የሚታየው?
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስድስት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 16 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚጎራበት ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ስድስት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸውን እና 14 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና አንድ የክልሉ ምክር ቤት አባል ተናገሩ።
ምርጫ 97፡ "የአዲስ አበባን ሕዝብ የከዳነው እኛ ነን ብዬ ነው የማስበው" ልደቱ አያሌው
በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ የዴሞክራሲ ብልጭታ የታየበት ነበር የሚባለው ምርጫ 97 ዋነኛ ተዋንያን ከነበሩት መካከል አቶ ልደቱ ይጠቀሳሉ። ከምርጫ 97 ባሻገርም አሁን ድረስ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙት አቶ ልደቱ ያንን ብዙዎችን ያነቃቃ እና በአጭሩ የተቀጨውን ምርጫ እንዴት ያስታውሱታል? በወቅቱ ያለፉባቸውን ውጣ ውረዶች እና ቁጭታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በተለይ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የፕሮስቴት ካንሰርን በተመለከተ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች
ይህ ከ40ዎቹ የዕድሜ ክልል በተሻገሩ ወንዶች ላይ የሚከሰተውን የካንሰር ዓይነት በተመለከተ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች እዚህ ቀርበዋል። የፕሮስቴት ካንሰር ምንድን ነው? ማን የበለጠ ተጋላጭ ነው? መከላከል ይቻላል? መልክቶቹ ምንድን ናቸው? ሕክምናስ አለው?
ምርጫ 97 ዘመናዊት ኢትዮጵያ ከገጠሟት አራት ታሪካዊ ዕድሎች አንዱ ነበር - ፕሮፌሰር መረራ
ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ውስጥ በርካታ ለውጦች እና ነውጦች ውስጥ አልፋለች። በተለይ ከንጉሡ ሥርዓት መውደቅ ጀምሮ የተለያዩ መሠረታዊ ለውጦችን ማምጣት ይችሉ የነበሩ አጋጣሚዎች ተፈጥረው ሥር ሳይሰዱ ባክነዋል። ከእነዚህ መካከልም የዛሬ 20 ዓመት ተስፋ በሚሰጥ ሁኔታ ተጀምሮ በግጭት እና በደም መፋሰስ የተጠናቀቀው ምርጫ 97 አንዱ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ፣ ሕዝቧ፣ ገዢው ፓርቲ እና ተቃዋሚዎች በጋራ መጎዳታቸውን ፕሮፌሰር መረራ በቁጭት ይናገራሉ።
ምርጫ 97፡ ከ20 ዓመታት በኋላ ሲታወስ
በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በብዙ መልኩ የተለየ የነበረው ምርጫ 97 ከተካሄደ እነሆ ዛሬ 20 ዓመቱን ደፈነ። ገዢው ኢህአዴግ 'እንከን የለሽ' ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ቃል መግባቱን ተከትሎ ተቃዋሚዎች ጥምረት ፈጥረው የተካሄደው ምርጫ ቃል እንደተገባለት ሳይሆን ቀውስን አስከትሎ ነበር የተጠናቀቀው። ኢትዮጵያም ወደ ዴሞክራሲ ልታመራ የምትችልበት ዕድል ጨንግፎ ኢህአዴግ ሁሉን ተቆጣጥሮ ወደ በለጠ ፈላጭ ቆራጭነት አመራ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ነጻ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንደናፈቀ ሁለት አስርት ዓመታት ተቆጠሩ።
የህወሓት መሰረዝ ውጤት ምንድን ነው? ቀጣይ መፍትሔውስ ምን ሊሆን ይችላል?
በአምስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲነት የመሰረዝ ዕጣ የገጠመው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት) በቀጣይ ምን አማራጭ አለው? የመሰረዙ ውጤትስ ምን ኣስከትልበታል?
ከየፈርጁ
ለልጆቻችን ዕድገት እና የአእምሮ ጤና ጠቃሚ መሆኑ እየተነገረለት ያለው ንጥረ ነገር
ኮሊን የተባለው ንጥረ ነገር ለሰውነት ጠቃሚ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች መካከል በዋናነት ይጠቀሳል። ኮሊን የሰው ልጆች አእምሮ በአግባቡ እንዲሠራ ይረዳል። የማሰላሰል ብቃትን በማሻሻል ከአእምሮ ዕድገት ጋር የተያያዙ ህመሞችን በመከላከልም እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ።
በዓለም ዙሪያ የኦቲዝም ክስተት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል? ወይስ ሌላ ምክንያት አለ?
ኦቲዝም ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እየታወቀ እንዲሁም ሰዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ነው። ይህ ግን ኦቲዝም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤም ፈጥሯል።
ሚሊዮኖች የደም ግፊት እንዳለባቸው አያውቁም፤ ከፍተኛ የደም ግፊት እንዳለብዎ ለማወቅ የሚረዳ ቀላል ዘዴ
በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው 1.3 ቢሊዮን ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የጤና ችግሩ እንዳለባቸው አያውቁም። በዓለም ጤና ድርጅት ደረጃ መሠረት የአንድን ሰው ለከፍተኛ የደም ግፊት ያለውን ተጋላጭነት ለማወቅ፣ የደም ግፊት ልኬት ንባብ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት እና ጤናን ለመጠበቅ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ለማወቅ ይህንን ዘዴ ይሞክሩ። ለቤትሰብዎ፣ ለጓደኞችዎ፣ ለሚያውቋቸው እና ጤና ለሚመኙላቸው በሙሉ ያጋሩ።
አጃኢብ!
245 ሚሊዮን ዶላር የመዘበሩት የቀድሞው የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር 10 ዓመት የጉልበት ስራ ተፈረደባቸው
245 ሚሊዮን ዶላር የመዘበሩት የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል 10 ዓመት ከባድ የግዳጅ የጉልበት ስራ ተፈረደባቸው።
'ሁሉም ዘመድ በሆነባት' ገጠራማ መንደር የተገኘ ነርቭን የሚያጠቃ ያልተለመደ በሽታ
በዘረ መል ለውጥ (genetic mutation) ምክንያት የሚከሰተው ይህ በሽታ የነርቭ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ቀስ በቀስ ሰውነትን ያዳክማል። በሽታው የሚከሰተው የተለወጠው ጂን ከሁለቱም ወላጆች ሲወረስ ብቻ ነው።
"ባሌ ለዓመታት በመድኃኒት እያደነዘዘ ይደፍረኝ ነበር"
ማታ ማታ ሻይ ውስጥ ማደንዘዣ መድኃኒት ይሰጣት እንደነበር አላወቀችም። መድኃኒት ሰጥቶ እያደነዘዘ ይደፍራታል። ድርጊቱን ከተናዘዘ በኋላ ኬት ፖሊስ ጣቢያ ብትሄድ ሕይወቱ እንደሚያበቃለት ስለነገራት ለፖሊስ ሳታመለክት ቀረች።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለማችን ወረርሽኝ ይሆናል ብለው ለምን ሰጉ?
ተመራማሪዎች ለወራት በእርሻዎች ላይ እየተስፋፋ ያለው የወፍ ጉንፋን ቀጣዩ የዓለም ወረርሽኝ ይሆናል በሚል የማስጠንቀቂያ ደወል እያሰሙ ነው። በሽታዎች እንዴት እንደሚጎለብቱ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች የወፍ ጉንፋን ልብ ሳንለው ወደ ሰዎች በመዛመት ወረርሽኝ ይሆናል በማለት አስጠንቅቀዋል።
የውሃ ኮዳችን ለበሽታ እንደሚያጋልጠን ልብ ብለዋል? እንዴት ማፅዳት አለብን? ምን ዓይነት ኮዳ እንጠቀም?
ከኮዳዎ ውሃ በተጎነጩ ቁጥር ወደ ውስጡ ባክቴሪያዎችን እያስገቡ እንደሆነ ያውቃሉ? ሥራ ቦታ፣ ስፖርት ቤት አሊያም በየዕለት እንቅስቃሴያችን የምንገለገልባቸው የውሃ ኮዳዎች ለጤና ቀውስ ሊዳርጉን ይችላሉ። ይህንን አስቀድሞ ለመከላከል ምን ማድረግ እንደሚገባ ተመራማሪዎች የሰጡትን ምክር እናካፍላችሁ።
አልኮል መጠጥ በጤናችን እና በዕድሜያችን ላይ የሚያስከትለው ጉድለት
የአልኮል መጠጦች ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ስፍራዎች ይጠጣል፤ የብዙ ድግሶች ማድመቂያ ተደርጎም ይወሰዳል። ሰውነትን ስለሚያፍታታ በቀላሉ ከሰዎች ጋር ለማውራት የሚጠቀሙበትም ሰዎች አሉ። ሲደሰቱ፣ ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ሲቀላቀሉ ወይም ሲያዝኑም ወደ መጠጥ ፊታቸውን የሚያዞሩ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ባለሙያዎች በየትኛውም መጠን የሚጠጣ አልኮል በጤና እና በዕድሜ ላይ ዳፋ አለው ይላሉ።
በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት ሁሉ ኪንታሮት ነው? ኪንታሮት ካልታከመ ምን ያስከትላል?
የፊንጢጣ ኪንታሮት ሰዎች ብዙም የማይነጋገሩበት ህመም ነው። አንዳንዶች ሐኪም ለማማከርም ሲያመነቱ ይስተዋላል። ለመሆኑ በፊንጢጣ አካባቢ የሚከሰት እብጠት እና ህመም ሁሉ ኪንታሮት ነው? ሕክምና የሚያስፈልገውስ መቼ ነው? ካልታከመስ ምን ያስከትላል?
በቀን ምን ያህል ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? ዓይነ ምድራችን ስለጤናችን ምን ያመለክታል?
እርስዎ በቀን ስንት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ይሄዳሉ? አንዴ? ሁለቴ? ወይስ አልፎ አልፎ? ለመሆኑ ዓይነ ምድር ስለ ጤናዎ ምን ያናገራል?
ስለምንመገበው ጥሬ ሥጋ ማወቅ ያሉብን ነገሮች እና ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
በዓላትን ከሚያደምቁ ነገሮች መካከል ምግብ እና መጠጦች ከፍ ያለ ድርሻ አላቸው። በተለይ እንደ ፋሲካ ያሉ ዓውደ ዓመቶች የሚመጡት ረዥም የጾም ወቅትን ተከትለው በመሆናቸው አቅም በፈቀደ ሁሉ እርድ ይከናወናል። በተለይ ደግሞ ጥሬ ሥጋ የበርካቶች ምርጫ ነው። ጥሬ ሥጋን በተመለከተ ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን?
ሌላ ዕይታ
ከማኅደራችን
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከበሮ እና ጽናጽልን ሌሎች ቤተ እምነቶች እንዳይጠቀሙ መከልከል ትችላለች?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የከበሮ፣ ጽናጽል እና መቋሚያ ንድፎችን በአዕምሯዊ ንብረትነት ማስመዝገቧን ተከትሎ ጉዳዩ ሲያከራክር ሰንብቷል። ምዝገባው ሌሎች ቤተ እምነቶች እነዚህን መገልገያዎች “እንዳይጠቀሙ የመከልከል መብት ይሰጣል ወይስ አይሰጥም?” የሚለው የክርክሩ ማጠንጠኛ ሆኗል። በዚህ ጉዳይ ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ኃላፊዎች ያላቸው አረዳድ እና የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን አቋም የተለያየ ነው።
ዕድገት በኅብረት ዘመቻ፡ የሦስቱ ጓደኛሞች የ50 ዓመታት ትዝታ
ወታደራዊው አስተዳደር ደርግ የአገሪቱን የመሪነት መንበር ከያዘ በኋላ የዛሬ 50 ዓመት የዕድገት በኅብረት ዘመቻን አወጀ። በዚህም ከ10ኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርስቲ ያሉ ተማሪዎች እና መምህራን በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተሰማርተው በማስተማር እና በልማት ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ አድርጎ ነበር። በዚህ ዘመቻ የተሳተፉ የዚያ ዘመን አፍላ ወጣቶች ከአምስት አሥርታት በኋላ በጋራ ተሰባስበው ያሳለፉትን ጊዜ አስታውሰዋል። ትዝታቸውንም ለቢቢሲ አጋርተዋል. . .
የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
የኢየሱስ ስቅለት እና ሞት በሕክምና ባለሙያዎች ዓይን እንዴት ይተነተናል?
በአይሁዶች እና ሮማውያን ችሎት ወንጀለኛ ተብሎ የቆመው ኢየሱስ ክርስቶስ በጥፊ ተመትቷል፣ ተገርፏል፣ ተራቁቷል፣ የእሾህ አክሊል ተደፍቶበታል። ኢየሱስ ከተያዘበት እስከ አርብ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ስቃይ ደርሶበታል። በዚህ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ብዙ ደም ፈስሶታል። ተጠምቷል። ከዚያም ሞቷል። የሕክምና ባለሙያዎች ኢየሱስ የደረሰበትን እንግልት፣ ድብደባ እና ስቅላት ከሙያቸው አንጻር እንዲህ ተንትነውታል።
'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
በአንድ ወቅት ኢትዮጵያ ክፉኛ አቁስላ፣ ማርካ ያከመችው የጁባላንዱ ፕሬዚዳንት ማዶቤ
"የብዙ ኢትዮጵያዊ ደም ነው የወሰደው። የኢትዮጵያ ደም ነው ያለህ እንለዋለን" ይህ በሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለአሁኑ የጁባላንድ ግዛት ፕሬዚዳንት ማዶቤ በቀልድ መልኩ ጣል ያደርጉላቸው ነገር ነው። ይህ በቀልድ የተለወሰ መሪር እውነታ ነው። እውነታው የሶማሊያዋን ራስ ገዝ ጁባላንድን ላለፉት 12 ዓመታት ያስተዳደረው ማዶቤ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ጦር ክፉኛ ቆስሎ በአዲስ አበባ ህክምና አድርጓል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
ሙዝ በዳቦ እየበሉ 'ፒኤችዲ' የሚማሩ የዩኒቨርስቲ መምህራን ሰቆቃ
ይህ ጥናታዊ ዘገባ የዩኒቨርስቲ መምህራን ላይ ያጠነጥናል፤ ከእነርሱም ውስጥ ፒኤችዲ (ዶክትሬት) የሚማሩት ላይ ያተኩራል። መምህራኑ የበለጠ በተማሩ ቁጥር የበለጠ እየተራቡ እንደሆነ ያወሳሉ። ቢቢሲ በርከት ያሉ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ለወራት ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ ቆይቷል። ከጉዳዩ ስፋት የተነሳ የብዙዎቹ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ እና ታሪክን በሚወክሉ በአምስት መምህራን ተወክሎ ቀርቧል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?