ማየት ለተሳነው አንበሳ የተደረገው የተሳካ የዐይን ቀዶ ሕክምና በሕንድ
ማየት ለተሳነው አንበሳ የተደረገው የተሳካ የዐይን ቀዶ ሕክምና በሕንድ
በምዕራብ ሕንድ ጉጃራት ግዛት ውስጥ ሐኪሞች በዐይን ሞራ ምክንያት ማየት የተሳነው አንበሳ ላይ የተሳካ ቀዶ ሕክምና አድርገዋል።
አንበሳው አድኖ ሊበላቸው የሚችላቸው እንስሳት ሳይቀር በአጠገቡ ሲንቀሳቀሱ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳያደርግ መቅረቱን ተከትሎ፣ ተይዞ በተደረገለት ምርመራ ነው ማየት እንደማይችል የታወቀው።
ከፍተኛ የሚባል የዐይን ቀዶ ሕክምና የተደረገለት አንበሳው ሰው ሰራሽ ሌንስም ተገጥሞለታል።