"ከብሔራዊ ቡድኑ ራሴን ያገለልኩት ለሌሎች ዕድል ለመስጠት ነው"፡ ሽመልስ በቀለ
ሽመልስ በቀለ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ15 ዓመታትን ተጫውቷል።
ኢትዮጵያ ከ31 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ስትሳተፍ የቡድኑ አባል ነበር።
እንደገና ከስምንት ዓመታት በኋላ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ስትሳተፍ፣ ሽመልስ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ነበር።
ከኢትዮጵያ አልፎ በግብጽ ክለቦች ለበርካታ ዓመታት የተጫወተው ሽመልስ፣ ግብጽ ላይ ያስቆጠራት ግብ ከማይረሳቸው የእግር ኳስ የደስታ ትዝታዎቹ መካከል ነች።
ሽመልስ አሁን "ለተተኪዎች ዕድል ለመስጠት" በማለት ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አግልሏል።
አጠቃላይ የእግር ኳስ ሕይወቱን በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጓል።