በቻይና መካነ እንስሳ ውስጥ ሰው ነው በሚል ውዝግብ ያስነሳው ድብ

በቻይና መካነ እንስሳ ውስጥ ሰው ነው በሚል ውዝግብ ያስነሳው ድብ

ይህ በምሥራቃዊ ቻይና ውስጥ በሚገኝ መካነ እንስሳ ውስጥ ያለን ድብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ጥያቄን አስከትሏል።

አንዳንድ ሰዎች የድቡን አቋቋም እና አካላዊ ገጽታን በመመልከት መካነ እንስሳው ድብ የሚመስል ልብስ የለበሰ ሰውን ድብ ነው በማለት ለዕይታ አቅርቧል በማለታቸው ውዝግብ ተነስቷል።

ነገር ግን መካነ እንስሳው ለጎብኚዎች የሚያሳየው እና በቪዲዮው ላይ የሚታየው እንስሳ እውነተኛ ድብ ነው በማለት ወቀሳውን አስተባብሏል። የእንስሳት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?