ከግብፅ ለባለቤታቸው ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ሚስት ጥፋተኛ ተባሉ

ናዲን ሜኔንዴዝ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, የ11 ዓመት እስር የተፈረደባቸው የድሞው ምክር ቤት አባል ሮበርት ሜኔንዴዝ ባለቤት ናዲን ሜኔንዴዝ

ከግብፅ መንግሥት ጋር በምሥጢር በመሥራት ጉቦ በመቀበል ተከሰው እስር የተፈረደባቸው የቀድሞው የአሜሪካ ምክር ቤት አባል ሮበርት ሜኔንዴዝ ሚስት በባለቤታቸው የረዥም ጊዜ የሙስና ተግባራት ውስጥ ተባባሪ በመሆን ጥፋተኛ ተባሉ።

የቀድሞው የኒው ጀርሲ እንደራሴ ሚስት የሆኑት ናዲና ሜኔንዴዝ በኒው ዮርክ ዳኛ ጥፋተኛ የተባሉት ባለቤታቸው ፖለቲካዊ ውለታ ለመዋል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ፣ ጥፍጥፍ ወርቅ እና ውድ ተሽከርካሪ ከተቀበሉባቸው እና ለዓመታት ሲፈጽሟቸው በነበሩት የጉቦ ወንጀሎች ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ነው።

የ58 ዓመቷ ናዲን ሜኔንዴዝ ጥፋተኛ የተባሉት ባለቤታቸውን በመደገፍ ጉቦ መቀበልን እና ፍትሕን ለማደናቀፍ መሞከርን ጨምሮ በ15 ክሶች ነው።

ግለሰቧ ክስ የተመሠረተባቸው ከባለቤታቸው ጋር ከሁለት ዓመት በፊት ቢሆንም የፍርድ ሂደቱ እንዲዘገይ የተደረገው በነበራቸው የጡት ካንሰር ሕክምና ምክንያት ነው።

ባለቤታቸው ሮበርት ሜኔንዴዝ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ላይ የ11 ዓመት እስር የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ለሰኔ ወር ቀጠሮ ይዟል።

በኒው ዮርክ የሚገኘው የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መግለጫ ባል እና ሚስቱ "ሥልጣንን ለብልሹ ጥቅም በማዋል" ተሳታፊ በመሆን "የወንጀል አጋሮች ናቸው" ብሏል።

ጨምሮም "የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመንግሥት ባለሥልጣናት የተሰጣቸውን ሥልጣን ለሽያጭ ማቅረብ እንደማይችሉ ግልጽ መልዕክት ያስተላለፈ ነው" ሲል ግለሰቦቹ ሥልጣንን ያላግባብ መጠቀማቸውን አመልክቷል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዋትስአፕ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በቀጥታ በዋትስአፕ ለማግኘት

ይህን በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ!

End of podcast promotion

በፍርድ ሂደቱ ወቅት ዐቃቢያነ ሕጎች ሚስት በባላቸው የጉቦ ድርጊቶች ውስጥ ወሳኝ ቦታ እንደነበራቸው የሚቀርቡ ሥጦታዎችን እና ገንዘብን የሚቀበሉት እሳቸው እንደነበሩ ለዳኛው አስረድተዋል።

ሚስት ጉቦዎችን ይቀበሉ ነበር በተባለበት ጊዜ ባለቤታቸው ሮበርት ሜኔንዴዝ ኃያል በሆነው የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ባለው የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ውስጥ ዲሞክራቶችን ወክለው ከአምስት ዓመታት በላይ ሠርተዋል።

የተከሳሿ ጠበቆች በቤታቸው ውስጥ የተገኘውን ወርቅ እና የገንዘብ ክምር "ከኃላፊነታቸው ጋር" የሚገናኝ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስጃ መንግሥት አላቀረበም ሲሉ ተከራክረው፣ ጥፋተኛ መባላቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

የምክር ቤት አባሉ ሜኔንዴዝ እና ሚስታቸው በአሜሪካ ምክር ቤት ውስጥ ባላቸው ሚና የመንግሥትን ሥልጣን በመጠቀም በምሥጢር የግብፅ መንግሥት ጥቅም በሚያስጠብቅ ሰፊ ተግባራት ውስጥ በመሳተፍ መከሰሳቸውን ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል።

መንግሥት ኒው ጀርሲ ግዛት ውስጥ በሚገኘው በግለሰቦቹ ቤት ውስጥ በ2022 በኤፍቢአይ በተደረገ ፍተሻ 100 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸው የወርቅ ጥፍጥፎች እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ማግኘቱን እንደማስረጃ አቅርቧል።

በተጨማሪም በባልና ሚስቶቹ እና በሌሎች ተባባሪዎቻቸው መካከል የተደረጉ የጽሁፍ ምልዕክት ልውውጦች እና ባል የቀድሞው የምክር ቤት አባል "አንድ ኪሎ ወርቅ ስንት ያወጣል"ሕንዳዊት ታዳጊ ንጹህ ውሃ እየጠጣች " loading="lazy" width="1360" height="765" style="aspect-ratio:1360 / 765" class="bbc-139onq"/>