የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ ከሌሎች መሪዎች ለምን የተለየ ሆነ?

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ ከሌሎች መሪዎች ለምን የተለየ ሆነ?

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተችበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ሦስት ዓመታት በታላላቅ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሳይቀር በተለየ አለባበስ የሚቀርቡት የፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አለባበስ አነጋጋሪ ሆኗል።

ዋይት ሐውስ ውስጥ ለምን ሥልጣናቸውን የሚመጥን ልብስ እንደማይልበሱ እና ሙሉ ልብስ እንዳላቸው የተጠየቁት ዜሌንስኪ በኃይለ ቃል ምላሽ ሰጥተዋል።

ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ እንደሌሎቹ የዓለም አገራት መሪዎች ለምድን ነው ሙሉ ልብስ የማይለብሱት?