የአየር ለውጥን በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል የተባለው የዕጸዋት ዝርያ
የአየር ለውጥን በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል የተባለው የዕጸዋት ዝርያ
የምድርን ሰባት በመቶ የሚሸፍነው ሊቸንስ የተባለው የዕጸዋት ዝርያ የአየር ሁኔታን እንደሚተነብይ ይነገራል።
ይህ ሊቸንስ የተባለው ዕጸዋት የሚፈጠረው ከፈንገስ እና አልጌ መዳቀል ሲሆን፣ እድገቱም አዝጋሚ እና አንዳንዱም በዓመት ከ1 ሚሊ ሜትር በታች ነው።
ይህ ዕጸዋት በሕይወት የሚቆዩበት ጊዜ ግን ዕድሜ ጠገብ ከሚባሉት ጋር የሚስተካከል ነው። አንዳንዶቹ እስከ 8600 ዓመት እንደቆዩ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።