እንስሳት የመሬት መንቀጥቀጥን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል ተፈጥሮ አላቸው?
በቱርክ እና ሶሪያ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እንስሳት ቀድመው የተለየ ባህሪይ አሳይተዋል የሚሉ ቪዲዮዎች በስፋት እየተዘዋወሩ ነው።
ይህ ውሻ ከርዕደ መሬቱ ቀደም ብሎ አሳይቶታል የተባለውን ሁኔታ የሚያሳየውን ቪዲዮ በአንድ ሌሊት ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተመልክተውታል።
በዚህም በርካታ ሰዎች ውሻ እና ሌሎች እንስሳት ይህ በአስር ሺዎችን ለሞት የዳረገው የመሬት መንቀጥቀጥ ከመከሰቱ በፊት ቀድመው የማወቅ ተፈጥሮ አላቸው ብለው ያምናሉ።
በእርግጥ እንስሳት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋን ቀድመው ማወቅ ይችላሉ? ይህንን በተመለከተ የእንስሳትን ባህሪይ በቅርበት የሚያጠኑ ባለሙያዎች ምን ይላሉ?