የኢትዮጵያ ከተሞች ስያሜ በሮም መገኘት ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ማለት ነው?
የኢትዮጵያ ከተሞች ስያሜ በሮም መገኘት ለትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ማለት ነው?
ሮም ውስጥ የተለያዩ ጎዳናዎች በኢትዮጵያ ከተሞች ስም ተሰይመዋል። አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞች በሮም ጎዳናዎች ላይ ተሰይመዋል። ጣሊያን ውስጥ ከከተሞቹ በተጨማሪ በአጼ ሚኒልክ እና በእቴጌ ጣይቱ ስምም የተሰየሙ ስፍራዎች አሉ።
ይህ ስያሜ በጣልያን ለሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምን ስሜትን ይፈጥራል? የሚለውን በተመለከተ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት ካርሜሎ ጆርዳኖ ወደ እነዚህ ስፍራዎች ሲሄዱ የሚፈጠርባቸውን ስሜት ለቢቢሲ አጋርተዋል።