ውፍረትን ለመቀነስ ሲባል የሚወሰዱ መድኃኒቶች በጤና ላይ ከባድ አደጋ እያስከተሉ ነው
ውፍረትን ለመቀነስ ሲባል የሚወሰዱ መድኃኒቶች በጤና ላይ ከባድ አደጋ እያስከተሉ ነው
ታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ክብደት ለመቀነስ በሚል ለሌላ ህክምና የተዘጋጀን መድኃኒት በመርፌ መውሰድ ተስፋፍቶ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ እየተነገረ ነው።
በኢንተርኔት አማካይነት በሕገወጥ መንገድ እየተሸጡ ያሉ የተለያዩ 'የክብደት መቀነሻ መድኃኒቶች' አንዳንዶችን ሸንቃጣ ሲያደርጉ፣ ሌሎች ላይ ደግሞ ለሕይወት አስጊ የሆነ ከባድ የጤና ችግርን እያስከተሉ ነው። እነዚህ መድኃኒቶች የትኞቹ ናቸው?