“አበበ ቢቂላ በዓለም የማራቶን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል” ጣልያናዊው ጋዜጠኛ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,
“አበበ ቢቂላ በዓለም የማራቶን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል” ጣልያናዊው ጋዜጠኛ

የአበበ ቢቂላ የሮም ኦሊምፒክ ድል በዓለም የማራቶን ታሪክ አዲስ ምዕራፍን የከፈተ ነው የሚሉት የጣልያን ታዋቂ የስፖርት ጋዜጣ ባልደረባ የሆኑት ቫሌሪዮ ፒቾኒ ስለ አበበ አውርተው አይጠግቡም።

በሮም ጎዳናዎች ላይ ሲመላለሱ ዘወትር አበበን እንደሚያስታውሱ የሚናገሩት ፒቾኒ በአፍሪካውያን የኦሊምፒክ ታሪክ ቀዳሚው የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊውን አትሌትን ሚዘክሩ ሁለት መጻህፍትን ጽፈዋል።

ፒቾኒ አበበ ቢቂላን በተመለከተ ዝርዝር ጥናት አድርገው ባዘጋጇቸው መጽሐፍቶቻቸው ላይ የአበበን ድል እና ከእሱ በኋላ የነበረውን ተጽእኖ በዝርዝር አቅርበዋል።

ታዋቂው ጋዜጠኛ ስለ አበበ ቢቂላ ድል እና በኦሊምፒክ መድረክ ላይ ያስከተለውን የአመለካከት ለውጥ እና ተከታታይ ድሎቹ ያስከተሉትን ተጽእኖን በተመለከተ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።