የሱዳን ጦርነት የቀሰቀሰው የዳርፉር የጅምላ ግድያ እና አስደንጋጩ ምስል
ሦስት ወር ያስቆጠረውን የሱዳንን ጦርነት ተከትሎ በዳርፉር ግዛት ውስጥ የጅምላ ግድያ እየተፈጸመ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣታቸው ዓለምን አስደንግጧል።
ለዚህ ደግሞ የሰዎች አስከሬን በብዛት ሜዳ ላይ እንዳልባሌ ነገር ሲጣል የተመለከተን አንድ ግለሰብ ለቢቢሲ ያየውን አነጋግሯል። የዚህ ሰው ምስክርነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ካወጣው ክስ ጋር ተመሳሳይነት አለው።
የመንግሥታቱ ድርጅት ሪፖርት እንደሚለው ከሆነ ማሳሊት በተባለው አካባቢ 87 ሰዎች በፈጥኖ ደራሽ ኃይል አባላት በጅምላ ተገድለዋል።
የሱዳን ጦር ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከባለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ ውጊያ ላይ ናቸው። ይህም በዳርፉር አዲስ ግጭት እና የጅምላ ግድያን ቀስቅሷል።